አለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት አከባበር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር አለም አቀፍ ኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንትን አከባበር ጋር በተያያዘ ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ስታፍ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የዓለም ኢንተርፕሪነርሽፕ ሳምንትን በማሰብ “ኢንተርፕሪነርሺፕ ለሁሉም” በሚል መሪቃል በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በተለያዩ ተግባራትን ማለትም ፡- 
Entrepreneurship Training Workshop(ETW) ለመምህራን ከህዳር 10-15/2017 ዓ.ም
Youth Entrepreneurship ለተመራቂ ተማሪዎች (ህዳር 14-15/2017 ዓ.ም) 
ለዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ፣ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች በPublic Entrepreneurship ዙሪያ ስልጠና በቀጣይ ሳምንት በመስጠት ሳምንቱን ለማክበር ታስቧል፡፡ 

የዘንድሮ የዓለም ኢንተርፕሪነርሽፕ ሳምንትን በሀገራችን ሲታሰብ ዋና ዓላማው ኢንተርፕሪነርሽፕ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ዜጎች ችግር ፈቺ አስተሳሰብ፣ ባህሪና ስነ ምግባር ተላብሰው ሥራ ጠባቂ ሳይሆኑ ችግሮችን ወደ ወርቃማ ዕድል በመቀየር ሥራ እና ሃብት ፈጣሪ እንዲሆኑ ማበረታታት ነዉ ተብሏል፡፡፡፡ 

ሁኔቱ ከህዳር 10 - 15/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል ፡፡

ዕውቀትን በተግባር!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

ህዳር 10/2017 ዓ.ም