በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ስራ ፈጣሪ ሴት ነጋዴዎች በዘመናዊ ሂሳብ አያያዝ እና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም በአጠቃላይ ንግድ አስተዳደር ዙሪያ አጭር ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ፡፡

በዛሬው እለት ህዳር 17 ቀን 2017 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና አዳራሽ ከዚህ ቀደም በሴቶች ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት የመሰረታዊ የንግድ ክህሎት ስልጠና ወስደዉ ለነበሩ እና በፕሮጀክቱ የሚሰጠዉን የንግድ ልማት አገልግሎት /BDS/ አገልግሎት ተጠቃሚ ለነበሩ ስራ ፈጣሪ ሴት ነጋዴዎች በዘመናዊ ሂሳብ አያያዝ እና ንብረት አስተዳደር እንዲሁም በአጠቃላይ ንግድ አስተዳደር ዙሪያ አጭር ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ፡፡
 ከዚህ በተጨማሪም ስራ ፈጣሪዎቹ ያለባቸዉን የፋይናንስ ችግር መቅረፍ የሚያስችላቸዉን በፕሮጀክቱ የሚቀርቡ የተለያዩ የብድር አማራጮችን በመጠቀም ያለባቸዉን ችግር መቅረፍ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ የተደረገ ሲሆን የክፍያ ፋይናንሲንግ ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ለስልጠናዉ ተሳታፊዎች ስለብድሩ ሁኔታና የአመላለስ ሂደቱ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ስልጠናውም ቀጥሎ ይውላል።