በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሎጅ ሲሰጥ የነበረው የEBMS ስልጠና ተጠናቀቀ።

በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የኢንተርፕረነርሺፕና የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና (EBMS)   ተጠናቀቀ፡፡ 

ይህንን ስልጠና በድሬ ዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚማሩ 33  ተመራቂ ተማሪዎች  ስልጠናውን ወስደዋል ። ስልጠናው ለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን በጥሩ ውጤት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዮት (EDI) የተዘጋጀውን ሰርተፍኬት የሚወስዱ ይሆናል።