በጋምቤላ ክልል የዜጎችን የስራ ፈጠራ ክህሎት ይበልጥ ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።


====================================
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት (ህዳር 07/2017 ዓ.ም) 
====================================

የኢፌዴሪ ኢንተርፕሩነር ሺፕ ኢንስቲትዩት ከክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባር ለ5 ዓመት በሚቆየውና SEED በሚባው ፕሮጀክት በክልሉ ለሚገኙ ለሥራ ፈላጊ ሴቶችና ወጣቶች፣ ገበሬዎች እና ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በመስራት ላይ ለሚገኙ አንቀሳቃሾች በንግድ ዕቅድ ዝግጅት፣ በንግድ አስተዳደር፣ በንግድ ሥራ ፈጠራ፣ በንግድ ክህሎትና መሰል ጉዳዩች ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በተስማመሙት መሠረት ከህዳር 07/2017ዓ.ም ጀምሮ በስድስት ዙር ለ240 ዜጎች የአንተርፕሩነርሽፕና ንግድ ሥራ ክህሎት ሥልጠና ንግድ ለመጀመር ለተዘጋጁ ሴቶችና ወጣቶች ስልጠና በኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰጠት ተጀመረ፡፡

የጋምቤላ ክልል የSEED ፕሮጀክት አስተባባሪና የEDI በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስተር አሰልጣኝ አቶ ሀምዲኖ ሚደሶ እንዳሉት ለአሁኑ ስልጠናው በጋምቤላ ከተማ የተሰጠ ቢሆንም በቀጣይ በሁሉም ወረዳ ተደራሽ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ ዋሲሁን እንዲሁም በኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክቱ ፎካል ፐርሰን ኢንስትራክተር ሳቢት ተማም እንዳሉት ስልጠናው ሥራ ፈላጊ ዜጋው እንዲሁም በስራ ላይ የሚገኙ በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ አንቀሳቃሾች ብሎም ገበሬዎች ሥራቸውን በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በክህሎትና ዕውቀት ላይ የተመሰረተ አሰራር እንዲከተሉ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ 

በመጨረሻም አቶ ሀምዲኖ ሚደሶ እንዳሉት ስልጠና የሚሰጣቸውን ዜጎች ከጋምቤላ ከተማ 5ቱም ቀበሌ ልየታ በማድረግና በማዘጋጀት በወቅቱ ላቀረበው የጋምቤላ ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ቢሮ መረጃዎች የሚከተሉትን ገፆች ይከታተሉ
ኢሜል bureauoflaborandskills@gmail.com
ፌስቡክ/Facebook https://www.facebook.com/gambella.bureau.of.labor.and.skills 
ቴሌግራም/Telegram https://t.me/gambella_BoLS                                
ዋትስአፕ/Whatsapp https://whatsapp.com/channel/0029VaDRcqN9MF930LQdoj0e
ቲውተር/Twitter https://x.com/labor2712?s=20