በሀረሪ ክልል  ሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEBMS ስልጠና መሰጠት ጀመረ።


የሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢንተርፕረነርሺፕና የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና (Entrepreneurship and Business Management Skill-EBMS) ተጀምሯል። በስልጠናው ላይ ተመራቂ ወጣቶች፣ ከሀረር  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ክወሊፍ ጤና ሳይንስ የተውጣጡ ቁጥራቸው 41 የሚሆኑ ሰልጣኞች እየተሳተፉ  ይገኛሉ። 

ስልጠናው ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ወጣቶች የእውቅና ሰርትፍኬት የሚበረከትላቸው ይሆናል።