በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI ) ለተከታታይ አራት ቀናት ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

 

ቆንዳ:- ህዳር 20/2017ዓ.ም (የገዋታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI ) ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቆንዳ እና በዶማ ማዕከል ከተለያዩ ቀበሌዎች ለተወጣጡ ወጣቶች በኢንተርፕርነር የንግድ አስተዳድር ችሎታ ( EBMS) ዙሪያ ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን የወረዳ ስራ፣ክህሎት ፣ንግድ ፣ገበያ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።

አቶ ተሻለ ክፍሌ የወረዳ ስራ፣ ክህሎት ፣ንግድ ፣ገበያ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ኃላፊ እንደገለፁት በሁለቱ ማዕከላት ከተለያዩ ቀበሌ ለተውጣጡ ወጣቶች ለተከታታይ አራት ቀናት ስሰጥ ቆይተው መጠናቀቁን የገለፁ ሲሆን የአቅም ግንባታ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና ወጣቶች ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንድገቡ የሚያነሳሳ ነው ብለዋሉ።

አክለውም በአካባቢያችን የሚገኙ ሀብቶችን በመጠቀም ገቢ ማግኘት እንደሚችሉና ከራሳቸውም አልፈው ለሀገራቸው ዕድገትና መለወጥ የራሳቸውን አሻራ ማስቀመጥ የሚችሉበት ስልጠና መሆኑን ተናግረዋሉ።

ወጣት አብረሃም አስፋው፣ መንግስቱ አጀቢ፣ ጉተማ ሙለታ እና ኤልያስ ከበባ በሰጡት አስተያየት ከስልጠናው ብዙ ግንዛቤና ዕውቀት እንደቀሰሙ ተናግረው በትንሽ ነገር ስራ ጀምረው ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚቻል ከስልጠናው ተረድተናል ያሉ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ክትትል ከተደረገ በስልጠናው ያገኘነውን ዕውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር በውጤት ለማሳየት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋሉ።

በመጨረሻም ለሠልጣኞች የዕውቅና ሠርተፊኬት በመስጠት የስልጠናው መረሃ ግብር ተጠናቀዋል።

ዘወትር:-ከኛ ጋር ስላሉ እናመሠግናለን!!

የገዋታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ!!

 

https://t.me/+tLjJ0y-WB7IyYmFk