በክረምት በጎ ፈቃድ ሰራዎች የታየውን እምርታ በበጋ በጎ-ፍቃድ እና በስራ ፈጠራ ዘርፍ መድገም እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር ገለፀ

በክረምት በጎ ፈቃድ ሰራዎች የታየውን እምርታ በበጋ በጎ-ፍቃድ እና በስራ ፈጠራ ዘርፍ መድገም እንደሚገባ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር የተጠናቀቀውን የክረምት በጎ ፍቃድ እና የአለም የኢንተርፕሪነሽፕ ሳምንት ማጠቃለያ ከኢንተርፕሪነርሺፕ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።

በእለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወ/ፃዲቅ የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር በክረምት በጎ-ፍቃድ ስራዎች በአስራስምንቱም ተግባራት ላይ በግንባር ቀደምነት መሳተፋን እና ለዚህም መምሪያው ዕውቅና መስጠቱን በመግለፅ በማህበሩ ደረጃ የተሳተፉ የክ/ከተማ ቅ/ፅ/ቤቶችን ለማመስገን መታሰብን ሲያበረታቱ በቀጣይ በሚደረጉ የበጋ በጎ ፍቃድ ተግባራትም ላይ በተሻለ ሁኔታ መስራት እና ከሁሉም በላይ በስራ ፈጠራ ረገድ ማህበሩ በትኩረት መሰራት እንዳለበት በመግለፅ መምሪያውም አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣት በቃሉ መሠረት በበኩላቸው ማህበሩ በክረምት የወጣቶች በጎፍቃድ ስራዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት መሰራቱን በመግለፅ በቀጣይም የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ለመስራት ማህበሩ አቅጣጫ መያዙን በማንሳት በተለይም በኢንተርፕሪነርሺፕ ዘርፍ ሀዋሳን የስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማዕከል ለማድረግ ከኢንተርፕሪነርሺፕ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት እና መሰል ተቋማት ጋር ማህበሩ በቅንጅት እንደሚራ ገልፀዋል።

በዕለቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣት ይሳቅ ሳንብሬ ወጣቶች በአደረጃጀት ታቅፈው ማህበረሰባቸውን በማገልገል ረገድ ማህበሩ ባለፉት ጊዜያት ሰፊ ስራ ሲያከናውን የቆየ አንጋፋ ማሀበር መሆኑን በማንሳት ከመሰል አደረጃጀቶች ጋር እንደፌዴሬሽን በመቀናጀት አመርቂ ስራ ሲሰራ መቆየቱን በመግለፅ በቀጣይም ሁሉም አደረጃጀቶች ተፈጥሯዊ ማንነታቸውን በጠበቀ መልኩ በፌደሬሽኑ ጥላነት ለከተማችን ወጣቶች የተሻለ ዕድልን በሚፈጥር መልኩ በቅንጅት እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በዕለቱም የአለም ኢንተርፕሪነርሽፕ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ስለ ስራ ፈጠራ ፅንሰሀሳብ በኢንተርፕሪነርሽፕ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት የሀዋሳ እና አካባቢው ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ተወካይ በሆኑን አቶ አብርሀም የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎችም በፕሮግራሙ ደስተኛ መሆናቸውን በማንሳት በቀጣይም መሰል የመነቃቂያ፣ አቅም ማጎልበቻ እና መመካከሪያ መድረኮች ተጠናከረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል።