ኢ.ዲ.አይ. ኢትዮጵያ በአርባ-ምንጭ ከተማ በሶስት ዘርፎች በድምሩ 68 ሰልጣኞች አስመረቀ።

በአርባ-ምንጭከተማ .ዲ.አይ. ኢትዮጵያ በሶስት ዘርፎች በድምሩ 68 ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡ የኢ..አይ. ኢትዮጵያ የሪጅናል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጌትነት ሳሙኤል ከእነዚህ 68 ሰልጣኞች ውስጥ 16ቱ በ EMPRETEC trainers 28 BOA trainers እና 24 EBMS trainers ስልጠናውን ወስደው መመረቃቸውን ገልፀዋል።

 
  አርባምንጭ:- ህዳር 14/2017 ዓ፣ም(አርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን

የኢ አይ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር / ሀሰን ሁሴን በዛሬው ዕለት በሶስቱ መርሃ ግብር ለተመረቁ አሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አክለውም .ዲ.አይ. ኢትዮጵያ እንደሀገር ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም በመፍጠር ሀገርን ለመገንባት ውጤታማ፣ ደፋር ችግር ፈቺ ዜጋ በማፍራት ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል እንደሚሰሩም ተናግረዋል። 

በመጨረሻም በእለቱ የተመረቁ ሰልጣኞች አይ ኢትዮጵያን አመስግነው በወሰዱት ስልጠና ባገኙት ክህሎት ማህበረሰብን ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡