ከአዲስ አበባ በ50 ኪ.ሜ ዙርያ ውስጥ በሚገኘዉ በሆለታ ከተማ ለ 60 ሴቶች የኢንተርፐረነርሽፕ እና የንግድ ክህሎት ልማት ሰልጠና በከተማዉ የባህል አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲቲዩት ስር የሚገኘዉ የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት-አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በህዳር ወርየሚከበረዉን የዓለም የኢንተርፐረነርሽፕ ወርና ሳምንት በአዲስ አበባ በሚገኙ 3 /ከተሞች በንግድ ክህሎት እና በሙያ ስልጠናዎች "ኢንተርፐረነርሽፕ ለሁሉም " በሚል መሪ ቃ ያከበሩ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከአዲስ አበባ በ50 . ዙርያ ውስጥ በሚገኘዉ በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በሆለታ ከተማ 60 ሴቶች የኢንተርፐረነርሽፕ እና የንግድ ክህሎት ልማት ሰልጠና በከተማዉ የባህል አዳራሽ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናዉ ላይ ስኬታማ የኢነተርፕረነሪ ባህሪያት፣ የንግድ ስራ ተግዳድሮቶችን መለየት እና የንግድ ስራ እቅድ አዘገጃጀት፣ የንግድ ስራ አመራር ፣በንግድ ስራ የሰዉ ሀይል አመራር እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝና መሰል ርዕሶች የተካተቱ ሲሆን ስልጠናዉ ከንድፈ ሀሳብ ባለፈ በተግባር የተደገፈ ግለታሪኮችን፣ ሚናዊ ጨዋታዎችን፣ ሰርቶ ማሳየት እንዲሁም የግል ምስከርነቶችን የያዘ ነበር፡፡

በስልጠናዉ ላይ ከሆለታ ከተማ እናት ባንክ የተገኙ ባለሙያዎች ከኢነተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስትቲዩት ጋር ስለሚሰሩት የብድር ማእቀፎችገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ ስልጠናዉ እስከሚጠነቀቅ ድረስ በሆለታ ከተማ የሚገኙ ሌሎች የገንዘብ ተቋማትም በወጣላችዉ መርሃ ግብር መሰረት ሰለ ተለያዩ የብድር አገለግሎቶች ለሴቶቹ ገለጻ እንዲያደርጉ ፕሮግራም የተያዘ ሲሆን የሆለታ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ እና የሙያ አንዲሁም የንግድ ጽህፈት ቤቶች ሰልጣኞችን በመመለመል እና በማስተባበር ከፍተኛ ሚና ተጫዉተዋል፡፡