The Global Entrepreneurship Week #GEW2024Ethiopia ceremony held on November 30, 2024 at Boditi Polytechnic College

The Global Entrepreneurship Week #GEW2024Ethiopia ceremony held on November 30, 2024 at Boditi Polytechnic College was a significant event. The program included a panel discussion, a certification program for EBMS TOT trainers and BDS TOA, and recognition certificates for Boditi Polytechnique College and Boditi City Enterprise Office.

የግሎባል ኢንተርፕርነሽፕ ሳምንት በሚል መሪ ቃል በቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በEDI ድርጅት አማካኝነት ከዚህ በፊት የተሰሩ ስራዎችን በሚመለከት የፓናል ውይይት ተካሄደ 

ቦዲቲ ፤ ህዳር ፤ 21/2017 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የግሎባል ኢንተርፕርነሽፕ ሳምንት በሚል መሪ ቃል በቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በEntrepreneurship Development Institute አማካኝነት ከዚህ በፊት የተሰሩ ስራዎችን በሚመለከት የፓናል ውይይት ተካሂዷል። አቶ ታረቀኝ መንግስት በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በዚህ የፓናል ውይይት መርሀግብር ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። አቶ ታረቀኝ በንግግራቸው Entrepreneurship Development Institute በከተማ አስተዳደሩ ከባለፉት አመታት ጀምሮ በሰዎች በተለይ በወጣቶች አመለካከት ዙሪያ ስሰራ የነበራቸው ስራዎች በገንዘብ የማይተመኑና ትልቅ ዋጋ ያላቸው እንደሆኑ ተናግሯል።

በዚህም በከተማችን ስራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ማህበራት ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ግለሰቦች እንዲሁም በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ያሉ ወጣቶች በቂ እውቀት እንዲያገኙ መደረጉን አውስተዋል። የቦዲቲ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከድርጅቱ ጋር በመሆን እነዚህ ሁሉ ስልጠናዎች በምቾት እንዲሰጡ ከፍተኛ አስተዋጾ በማበርከቱ በከተማ መንግስት ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። አቶ እዮብ ብርሃኑ የቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ዲን በበኩላቸው Entrepreneurship Development Institute አማካኝነት የሚሰጡ ስልጠናዎች የሰዎችን ህይወት በበጎ ጎኑ የሚቀይሩ እንደሆኑ አንስተዋል። ከተማ ማህበረሰብ ይህንን መልካም አጋጣሚ በስፋት መጠቀም እንዲችል በቀጣይ ጊዜያት ከከተማ እስከ ቀጠና አሰቀድሞ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ፕሮግራሙ በባለፉት ጊዜያት በEBMS (Entrepreneur Business Management Skills) TOT and BDS (Business Development Service) TOA የሰለጠኑ ሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፍኬት ሽልማት መሰጠት ችሏል። በተጨማሪም EDI ድርጅት በከተማው የተሰጡ የተለያዩ የክህሎት ስልጠናዎች በስኬት እንዲጠናቀቅ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለቦዲቲ ከተማ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት እንዲሁም ለቦዲቲ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ልዩ የእውቅና እና የሰርትፍኬት ሽልማት ሰጥቷል።

Entrepreneurship Development Institute (EDI) - Ethiopia : Inspire, Disrupt, Transform 

#GEW2024Ethiopia