ከስራና ክህሎት ሚንስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ እትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ጉብኝት ተደረገ

ከስራና ክህሎት ሚስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ እትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ጉብኝት ተደረገ ። የዚ ጉብኝት አላማውም ባለፈው አመት በተደረገው ጉብኝት እና ግምገማ የታዩትን ጥንካሬዎች እና ክፍተቶችን ከምን እንደደረሱ እና አዳዲስ የተሰሩ ስራዎችም ካሉ እነሱን ለማየት ታስቦ የተደረገ ጉብኝት ነበር  ። በተደረገውም ግምገማ ከዚ በፊት የታዩ እና የቀጠሉ ጥንካሬዎችን እውቅና የተሰጠ ሲሆን በታዩት ክፍተቶች ላይም የማሻሻያ ሃሳቦች እና ሂሶች ተሰቶባቸዋል ። 

በተጨማሪም ከየተቋማቱ በተውጣጡ ተወካዮች በዞኑ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የቴክኒክ እናሙያ አንድ ማእከላት እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ  የስራ አፈጻጸም የቀረበ ሲሆን በግምገማውም የታዩ ክፍተቶች በአፋጣኝ እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡