ለ15 ሴት ስራ ፈጣሪዎች የገበያ ትስስር መፍጠሩን ኢ ዲ አይ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።

 አርባምንጭ፣ህዳር 2017 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን) 

በኢ ዲ አይ ኢትዮጵያ የEDI-WEDP ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ለ15 ሴት ስራ ፈጣሪዎች የገበያ ትስስር በአርባምንጭ ከተማ በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛር በመሳተፍ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን የገበያ ትስስር እንደተፈጠረላቸው የኢ ዲ አይ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ ቅርንጫፍ አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሪት ሙሉወርቅ በቀለ ገልፀዋል።

ተቋሙ ውጤታማ ስራ ፈጣሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም በመፍጠር ውጤታማ፣ ደፋር ችግር ፈቺ ዜጋ በማፍራት ከራሳቸው አልፎ ለሌሎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማስቻል መሆኑንም ተናግረዋል።

አክለውም አስተባባሪዋ ለስራ ፈጣሪዎች የክህሎት መር ስልጠናዎችን በመስጠት የገበያ ትስስር በመፍጠርና ብድር አቅርቦት በማመቻቸት እንዲሁም ድጋፍና ክትትል በማድረግ በከተማው የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ከኢንተፕራይዝና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም አስረድተዋል።