A panel discussion held at Central Hotel Hawassa in Sidama Regional State

Today on November 20, 2024, there was a half-day panel discussion held at Central Hotel Hawassa in Sidama Regional State. 85 participants from TVTs, NGOs, Hawassa University, and other public organizations attended the event. 

Panel discussion that was fully organized by EDI-Ethiopia primarily focused on the opportunities and challenges young entrepreneurs faced and the role of TVTs in entrepreneurship development.

"Entrepreneurship is for Everyone"

"ኢንተርፕረነርሺፕ ለሁሉም" በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም ዓቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በሀዋሳ ከተማ ተከበረ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ዓለም ከቀፉን የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በሀገራችን ለዘጠነኛ ጊዜ በማክበር ላይ ሲሆን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከሀዋሳ ከተማ ስራ አሰሪና ሰራተኛ መምሪያ ጋር በመሆን በዓሉን በልዩ ልዩ መረሃግብሮች አክብሯል።

በመረሃግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪና ሰራተኛ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ጥላሁን ሀገር ለተያያዘችዉ ሁሌንተናዊ ብልፅግናና የስራ አጥ ቅነሳ ስትራቴጂ የኢንተርፕርነርሽፕ /የስራ ዕድል ፈጠራ/ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱን አንስተዉ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደርም በዘርፉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉን ገልፀዋል።

በሀዋሳ ከተማ ከዚህ ቀደም በዘርፉ የነበሩ ክፍተቶች የስራ አጡን ቁጥር ከፍ ያደረጉ ፤ አዳዲስ ኢንተርፕርነሮች እንዳይኖሩ መንገድ የዘጉና ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ጭምር መንስኤ ሆነዉ የነበሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ታሪኩ የከተማ አስተዳደሩና የክልሉ መንግስት በወሰዱት ጠንካራ ሪፎርም አሁን ላይ ዉጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈጠራ መር የኢኮኖሚ ሥርዓትን ዕውን ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ከኢትዮጵያ ኢንተርፕነር ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸዉን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩት ሲዳማ ክልል አስተባባሪ አቶ ጌትነት ሳሙኤል በበኩላቸው ሀገራችን ኢንተርፕረነርሺፕን ተጠቅማ ብልፅግናዋን እውን እንዲታደርግ ለኢንተርፕሩነሮች ምቹ ስነ ምህዳር መገንባት አለባት ብለዉ የስራና ክህሎትን ጨምሮ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸዉ አስረድተዋል፡፡

ለኢንተርፕሪነርሺፕ የተሻለ ትኩረት የሰጡ ሀገራት የተሻለ ኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት ችለዋል ያሉት አስተባባሪው በሀገራችን በአሁኑ ወቅት ያለዉ መነሳሳት ዉጤት እያስመዘገበ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢንስቲዩቱ ከሀዋሳ ከተማ ስራ አሰሪና ሰራተኛ መምሪያ ጋር በመተባባር በከተማ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸዉን ተናግረዉ ዓለም ዓቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ከህዳር 9 እስከ 17/2017 ዓ.ም ከመምሪዉ ጋር በመሆን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በፓናል ውይይትና የዕዉቅና መረሃግብር መከበሩን አስታዉቀዋል።

ዓለም አቀፉ የሥራ ፈጣሪዎች ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 15ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለዘጠነኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።

በማዕከሉ አሰልጣኝና የስልጠና አስተባባሪ የሆኑት ጽጌረዳ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው ማእከሉ ለስራ ፈጣሪ ወጣቶትና ሴቶች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እና ልዩ ልዩ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን የበለጠ ለማጎልበትና ወደ ውጤት ለመቀየር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።