የኢፌዴሪ ኢንተርፕርነርሺፕ ኢንስቲትዩት ከክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባር ሁለተኛ ዙር ስልጠና ለሥራ ፈላጊዎች በጋምቤላ ከተማ ተደራሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

 

====================================

የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት (ህዳር 15//2017 ዓ.ም)

====================================

የኢፌዴሪ ኢንተርፕሩነር ሺፕ ኢንስቲትዩት ከክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባር ለ5 ዓመት በሚቆየውና SEED በሚባው ፕሮጀክት በክልሉ ለሚገኙ ለሥራ ፈላጊ ሴቶችና ወጣቶች፣ ገበሬዎች እና ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው በመስራት ላይ ለሚገኙ አንቀሳቃሾች በንግድ ዕቅድ ዝግጅት፣ በንግድ አስተዳደር፣ በንግድ ሥራ ፈጠራ፣ በንግድ ክህሎትና መሰል ጉዳዩች ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት በተስማመሙት መሠረት ከህዳር 07/2017ዓ.ም ጀምሮ በስድስት ዙር ለ240 ዜጎች የአንተርፕሩነርሽፕና ንግድ ሥራ ክህሎት ሥልጠና ንግድ ለመጀመር ለተዘጋጁ ሥራ ፈላጊ ዜጎች ስልጠና በኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመስጠት ባቀደው መሠረት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተደራሽ ተደርጓል፡፡

በኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፕሮጀክቱ ፎካል ፐርሰን ኢንስትራክተር ሳቢት ተማም እንደገለጹት በሁለተኛ ዙር በጋምቤላ ከተማ ከአምስቱም ቀበሌ ከተወጣጡ 40 ሴቶችና 8 ወንዶች በድምሩ ለ48 ሥራ ፈላጊ ዜጎች የአንተርፕሩነርሽፕና ንግድ ሥራ ክህሎት ሥልጠና ተደራሽ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል የSEED ፕሮጀክት አስተባባሪና የEDI በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስተር አሰልጣኝ አቶ ሀምዲኖ ሚደሶ በበኩላቸው እንዳሉት ገና ስልጠናው 4 ዙርየሚቀረውና ስልጠናው በተከታታይ በከፍተኛ ደረጃ በሰለጠኑ ባለሞያዎች የሚሰጥሲሆን ይህም ሥራ ፈላጊ ዜጋው በቀላሉ ሥራን መፍጠርና ንግዱ ዕቅድ የማዘጋጀት ዕውቀትናክህሎቱን እንደሚያሳድግለት ገልፀዋል፡፡

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ቢሮ መረጃዎች የሚከተሉትን ገፆች ይከታተሉ

ኢሜል bureauoflaborandskills@gmail.com

ፌስቡክ/Facebook https://www.facebook.com/gambella.bureau.of.labor.and.skills

ቴሌግራም/Telegram https://t.me/gambella_BoLS

ዋትስአፕ/Whatsapp https://whatsapp.com/channel/0029VaDRcqN9MF930LQdoj0e

ቲውተር/Twitter https://x.com/labor2712?s=20