የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዮት አለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንትን "ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል።

የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዮት አለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንትን "ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል።
ይህንን የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንት በማስመልከት በአዲስ አበባ በሶስት የስልጠና ቦታዎችላይ የኢንተርፕርነርሽፕ ባህሪያትን እንዴት መላበስ እንችላለን በሚል ርእስ እንዲሁም ከዚህ በፊት የፕሮጀክቱ አገልገሎት ያገኙ እና ስኬታማ የሆኑ ሴቶች ልምዳቸውን ለሰልጣኞቹ በሚያካፍሉበት ፕሮግራሞች ታጅቦ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 7(እምርታ የግል አሰልጣኝ) ከህዳር 2 እስከ 6/2017 .ም  ለ77 ሴቶችበተሰጡት መሰረታዊ ኢንተርፕነርሽፕ ስልጠናዎች ላይ የቢዝነስ ባለቤቶች አጠቃላይ ቢዝነሳቸውን እንዴት ነው የሚስተዳድሩት? አዳዲስ ሀሳቦች እንዴት ነው የሚያመነጩት? የገበያ ጥናት ፤የሂሳብ መዝገብ አያያዝ አንዲሁም የደንበኛ አያያዝ ላይ ሰልጣኞች ሀሳባቸውን እንዲለዋወጡና በየቡድናቸው ሆነው ወይይት እንዲያደርጉ ተደርጓል ፡፡

በሌላ ዜና በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከጥቅምት 28/2017 .ም ጀምሮ 35 ሴቶች የዳቦ እና ኬክ ስራ ስልጠና የጀመረ ሲሆን ይም ለአንድ ወር 15 ቀን የሚቆይ ይሆናል።